ABOUT


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እኔም ወደናንተ እስክመጣ ድረስ ፤
ያቅሜን ሰርቻለሁ መቼም አልወቀስ ፤
ሐውልት አቁሜአለሁ ይሁን ማስታወሻ ፤
ለሚመጣው ትውልድ ስማችሁን ማንሻ !


ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ

የብሉያት እና የአዲሳት መምህር በእየሩሳሌም ከ50 ዓመታት በላይ የቆዩ አባት ናቸው።በጵጵስና መአረግ ከመሾማቸው በፊት ገዳሙት በመጋቢነት አስተዳድረዋል ። ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በአረቢኛ እና በእብራይስጥ ቋንቋ የተጻፉትን ቅዱሳት ታሪካዊ ቦታዎች ወደ አማርኛ በመተርጎም፤ከቦታው ጋር የሚዛመዱትን ጥቅሶች ከመጸሐፍ ቅዱስ አውጥቶ በማዘጋጀት ፤ በግዕዝ ቋንቋ የተጻፉትን ወደ አማርኛ በመተርጎም እና ቅዱሳት ታሪካዊ ቦታዎችን ዞረው በማሳየት እንዲሁም ጽሑፌንም በማረም ታላቅ እገዛ አድርገውልኛል ።





ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ

ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በኢየሩሳሌም ገዳም ሁሉት ጊዜ ተሹመዋል።በኢየሩሳሌም ሆነው ባስፈሪው ዘመን መንግሥቱ ኃይለ ማርያም አስተዳደር ለረሸናቸው 60 ሚንስተሮች እና ለአለቁት ወጣቶች ሁሉ ስርዓቱን አውግዘው እና ተቃውመው ደብዳቤ ከጻፉት ከሁለቱ ሊቀ ጳጳሳት አንዱ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ናቸው። የሚሰራውን በመርዳት፤ በማሰራት እና በማስተባባር እግዚአብሔር ጸጋውን የሰጣቸው አባት ነበሩ።አባታችን ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በየሩሳሌም እና በኢትዮጵያ ታሪክ የማሽራችውን ሥራዎች ሰርተዋል ። በኢየሩሳሌም ከሰሯቸው ሥራዎች መካከል አንዳንዱን በመጽሐፉ ውስጥ ጠቅሻለው።እኔም መጽሐፍን ሳዘጋጅ ማስረጃዎችን በመስጠት እረድተውኛል ። በአደረባቸው እመም ምክንያት እኝህ መልካም አባት ከዚህ ዓለም ጥቅምት 30 ቀን 1996 ዓ.ም አርፈዎል ።

ብፁዕ አቡነ አብሳዲ

በኢየሩሳሌም ከ60 ዓመታት በላይ የቆዩ አባት ናቸው።በጵጵስና መአረግ ከመሾማቸው በፊት ገዳሙት በመጋቢነት አስተዳድረዎል።ለመጸሐፉ ታሪካዊ ቦታዎች እና አገሮች የት እንደሚገኙ በካርታዎች ላይ ያለውን ሰሞች ወደ አማርኞ ተርጉሜ ላቀረብኩት በአረቢኛ እና በእብራይስጥ (በሂብሩ) ቋንቋ ከተጻፉትን ቅዱሳት ታሪካዊ ቦታዎች ጋር በማዛመድ እርማት በመስጠት እና በጥሩ ሁኔታ ይበልጥ በማዘጋጀት ፤ ጽሑፌንም አንብቦ በማረም በቪዲዮ እና በሲዲዎሽ እየተዘጋጀ ላለው ፊልም በመተባበር ቅዱሳት ታሪካዊ ቦታዎችን ዞሮ በማሳየት ታላቅ እርዳታ አድርገውልኛል ።




አባ/መጋቢ/ብርሃነ መስቀል ገ/ጽዮን

በኢየሩሳሌም ከ57 ዓመት በላይ የቆዩ እና በገዳሙ መዝገብ ቤት ለብዙ ዓመታት ያገለገሉ አባት ነበሩ።የዴር ሱልጣንን ጉዳይ በሚመለከት የታሪክ እና ሌሎችንም የታሪክ ማስረጃዎች በገዳሙ መዝገብ ቤት ጠብቀው አቆይተዋል።አባ/መጋቢ/ ብርሃነ መስቀል ግ/ጽዮን በገዳሙ መዝገብ ቤት ለብዙ ዓመታት በመስራታቸው እያንዳንዱን ማስረጃ ዋንውን እና ቅጅውን በጥንቃቄ የሚያውቁ እና የያዙ አባት ነበሩ። የዴር ሱልጣንን ታሪክ በሚመለከት ለተዘጋጀው ጽሁፍ ይበልጥ ለአንባቢው ግልጽ እንዲሆን በማንበብ እና በማረም እረድተውኛል። ለብጹዕ አብነ ፊሊጶስ ስለዴር ሱልጣን በአዘጋጁት መጽሕፍቶች ላይ በጃቸው ስለዴርሱልጣን የተጻፉትን ግልባጭ በስጦታ አበርክተውልኛል።





መ ግ ቢ ያ

የኢየሩሳሌም ታሪክ ለኔ ከህጻንነቴ ጀምሮ እየሰማሁና ቅዱሳት የታሪካዊ ቦታዎችን ጭምር በፎቶግራፍ እያያሁ ነው ያደኩት ። አያቴ ማንያህልሻል ዋካ ከ 50 ዓመት በፊት ኢየሩሳሌም ነበረች። አክስቶቼ እና አጎቴም እዛ ለብዙ ዓመታት ነዋሪዎች ናቸው ። ከአባቴ ወገን የሆኑት ኢየሩሳሌምን ሊሳለሙ ሄደው ከሦስቱ አንዱ ሲመለስ ሁለቱ ግን መንገድ ላይ ሞተዋል ። ይህ የሆነው በ1910 ዓ.ም አካባቢ ይሆናል። የተመለሱት ወልደ ሰማዕት ይባላሉ ።

የሳችው እና የሌሎቹም ወደ ኢየሩሳሌም የመጡ ተሳላሚዎች ስም ዝርዝር የመጡበት ቦታ፤ የፈጀባቸው ወራቶች ሳይቀር አባ/መጋቢ/ብርሃነ መስቀል ገ/ጽዮን ተጠርዞ በተዘጋጀው መዝገብ ውስጥ ይገኛል። ጊዜ እና ሰዓቱ ሲደርስ እኔም ወደ ኢየሩሳሌም ሄድኩ። አራት ወር እንደቆየሁ የመጽሐፉን ሥራ ከብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ እና ከብፁዕ አቡነ አብሳዲ ጋር “ሀ” ብዬ ጀመርኩ። ለሁለት ዓመት ከአራት ወር በላይ በወር ቢያንስ 2 ጊዜ ስንጓዝ ማስታወሻ በመያዝና በቪዲዮ በመቅረጽ ጀመርኩ ። አቡነ ሕርያቆስም ሆኑ አቡነ አብሳዲ አረብኛውንና እብራይስጥ ቋንቋ (ሂብሩ) አሳምረው ስለሚያውቁት ስለቅዱሳት የታሪካዊ ቦታዎች የተጻፉትን መጻሕፍት ለምስክርነት እየገዙ ማንበብ ጀመሩ ።

በሄድንበት ቦታ ሁሉ ችግር አላጋጠመንም።በይበልጥ አቡነ ሕርያቆስ በገዳሙ ያሉትን አባቶች ከ50 ዓመታት በፊት ጀምሮ ስለሚያውቋቸው በሄድንበት ቦታ ሁሉ በክብር ይቀበሉን ነበር ። መጀመሪያ ያሳተምኩት መጽሐፍ ሊይዝ የሚገባውን እና ማብራራት ያለበትን አካቶ አለመያዙን ተረዳሁ ። ሊቀ መዕመራን ቄስ ዶ/ር አማረ አሜሪካ ጋብዘውኝ፤ ሊቀ ሊቃውንት መምህር ወርቅነህ ኃይሌ መኖሪያ ፈቃድ እዳገኝ ረድተውኝ በአሜሪካ መኖር ከጀመሩኩ በኋካ ነው ሁለተኛውን የመጽሐፍ ሥራ የጀመርኩት ።

በዚህ የተነሳ በእስራኤል ዮኒቨርሲቲ ውስጥ በግላቸው እንኳን እነዚ ቦታዎች ቢቆፈሩ ማስረጃ ይገኛል በማለት አስተያየታቸውን ይሰጡ ነበር።ስለ ቅዱሳት ታሪካዊ ቦታ ሲያስረዱና ሲያስተምሩ ተራውን ሰው ምሁር ማድረግ ይችሉ ነበር ። መጽሐፉን ሳዘጋጅ እስከ መጨረሻው የረዱኝን ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ፤ብፁዕ አቡነ አብሳዲ፤ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፤አባ/መጋቢ/ብርሃነ መስቀል እና ፕሮፌሰር ኪርስቲን እስቶፈርጌን የመጽሐፉን ፍጻሜ ሳላሳያቸው በሞት ስለተለዩኝ ከልቤ አዝኛለሁ።በሕይወት የቀረሁት እኔ ብቻ ሆንኩ።እግዚአብሔር ረዳኝና እንደገና በአዲስ መንፈስ ተነስቼ መጽሐፉን ጨረስኩት።